ስለ ከተሞቻችን እናስብ
ከተሞቻችን በመጠኑም ቢሆን እየሰፉ መሆናቸው አይካድም። ከአዲስ አበባ ጀምሮ በቅርቡ እስከተመሰረቱ አዳዲስ ከተሞች ድረስ ሁሉም ያቅማቸውን ያክል እየሰፉ እንዲሁም በመጠኑ እያደጉ ነው። እድገትና ስፋት ሲኖር ደግሞ ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ከተማ መፍለስ ይጀምራሉ። ሆኖም ከተሞቹ ለኗሪዎች ምቹና ተስማሚ እንዲሆኑ ማድረግ ለነገ ማይባል ጉዳይ ነው። ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ ግን፤ ባብዛኛዎቹ ከተሞቻችን ላይ የተለያዩ አደጋዎች ተጋርጠውባቸዋል።
ስለሆነም ከዘሬ ጀምሮ የተለያዩ ከተሞቻችንን ምን አይነት ችግር አለባቸው፣ ምንስ አይነት መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል የሚሉ ሃሳቦችን እናቀርብላችኋለን። እናንተም ያላችሁን አስተያየት እና መረጃ ታካፍሉን ዘንድ እንጠይቃለን። ዛሬ ሁሉንም ማንሳት ባንችልም፣ አንዳንድ የከተሞቻችን ችግሮችን እናነሳለን።
ስለሆነም ከዘሬ ጀምሮ የተለያዩ ከተሞቻችንን ምን አይነት ችግር አለባቸው፣ ምንስ አይነት መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል የሚሉ ሃሳቦችን እናቀርብላችኋለን። እናንተም ያላችሁን አስተያየት እና መረጃ ታካፍሉን ዘንድ እንጠይቃለን። ዛሬ ሁሉንም ማንሳት ባንችልም፣ አንዳንድ የከተሞቻችን ችግሮችን እናነሳለን።
ስለ ባህር ዳር
ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ ባሕርዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕርዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ምንጭ (http://www.mwud.gov.et)
በመጀመሪያ በባህር ዳር ከተማ የተመለከትኋቸውን ላውራ።
1ኛ. የጸጥታ (በተለይ የዝርፊያ) ችግር
2ኛ. የመብራት ችግር
3ኛ. የአቅጣጫ ተቋሚ ችግር
4ኛ. ተስማሚ የመገበያያ ቦታ ችግር እና ሌሎችም ናቸው።
1ኛ. የጸጥታ (በተለይ የዝርፊያ) ችግር
2ኛ. የመብራት ችግር
3ኛ. የአቅጣጫ ተቋሚ ችግር
4ኛ. ተስማሚ የመገበያያ ቦታ ችግር እና ሌሎችም ናቸው።
1ኛ. የጸጥታ (በተለይ የዝርፊያ) ችግር
ሰሞኑን በበህርዳር የዝርፊያ ወሬ በየቦታው መሰማት ጀምሯል። ዐይን ያወጣ ፣ ጥርስ ያገጠጠ ባደባባይ እየደበደቡ ከኪስ በማውጣት መሮጥ የተለመደ ሆኗል። የዚህን ዝርዝር ጉዳይ ማለትም እንዴት አይነት ዘዴ ይጠቀማሉ፣ ብዛታቸው በግምት ምን ያህል ይሆናሉ፣ አሰልጣኝ ያላቸው ስለመሆኑ፣ ፖሊስስ በዚህ ጉዳይ ምን እያደረገ እንደሆነ እና ሌሎችንም ጉዳዮች በቅርቡ እናቀርባለን። ይጠብቁን!